የግንባታ ሁኔታ
የግንባታ ሁኔታ
በሂደት ላይ
የፍቃድ ሁኔታ
በጥብቅ ላይ
የቦታ ሁኔታ
1840 ካሬ ሜትር
በጀርመን አገር በኮለን ከተማ የምትገኘው ርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከዛሬ ቀደም ከነበራት ርስት የቦታ ባለቤትነት በእግዚአብሔር ፈቃድ ተጨማሪ የአምልኮ ፣ የበረከት ፣ የባለቤትነት ዕድሉን አምላከ ሚካኤል አሳክቶላት ከኃይል ወደ ኃይል ፣ ከበረከት ወደ በረከት ፣ ከትጥበት ወደ ስፋት ለመሻገር በባዕድ አገር ሰፊ የቦታ (1840 ካሬ ሜትር) ባለቤት ሆናለች ።
የቤተክርስትያናችን የቦታ ግዢ ከተፈፀመ በኃላ በተያዘው እቅድ መሰረት የውስጥ ማሰፋፋት ለማድረግ አስፈላጊው ጥናት ለማድረግ ከአርክቴክት ጋር የመግባቢያ ውል ተፈርሞ ሰራው ተጀምሯል ቤተክርሰትያናችን በቅርሰነት ሰለተመዘገበ አፍርሶ መስራት ሰለማይቻል የቤተክርሰትያኑን ንድፍ ለማውጣት አስቸጋሪ ነበር። ሆኖም አስፈላጊው የግንባታ ሂደት አልፎ ለሚመለከታቸው የመንግሰት አካላት (Stadt Köln Bauamt) የመጀመሪያውን ማመልከቻ ( Bauantrag ) ተደርጐ ነበር ። ሆኖም ፍቃድ አግኝተን ለመስራት ከጐረቤቶቻችን ያለው እርቀት አስፈላጊ ነበር ይህም ምንአልባተ ግንባታው ሲጀመር በወሰን የሚጋሩን ጐረቤቶቻችን ቦታ ላይ ሊነካ ስለሚችል ( Baulast) የእነሱን ይሁንታ ማግኘት ነበረብን ነገር ግን ጐረቤቶቻችን ለዚህ ብዙ ገንዘብ ሰለጠየቁን ይህን ለማሰቀረት ከ Bauphysik ጋር በመመካከር Baulast ፕላኑ በውስጥ እንዴሆን ተደርጓል ከዚህ በተጨማሪ የመጀመሪያውን ቤተክርስትያን ግዢ ሲደረግ በፊት በኩል ባለው ጓሮ ቦታ ባለቤትነቱ የአኢቫንኬልሽ ቤ/ክረስትያን ይዞታ ሰለነበር ይህንም ቦታ ግዢ ተፈፅሞ የኖታሩ እማኝ አባሪ ተደርጐ ይህ ማሻሻያ የተደረገበት ማመልከቻ በድጋሚ ለStadt Köln Bauamt ተመልክቷል።
የእንፃ መስሪያ እቅድ(Bauplan)ማሻሻያ በተደረገ ቁጥር ለአርክቴክቶሮቹ የሚከፈለው ገንዘብ እና ለቦታው መስሪያ ፍቃድ የማግኛው ጊዜ ብዙ ጊዜ ፈጅቷል ። አሁን የመስሪያ ፍቃድ ለማግኘት እየጠበቅን እንገኛለን::
