
ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት የኮሎኝ ርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ይፋዊ ድረ ገጽ ነው።

አሁን በመላው አውሮፓ፥ በአፍሪካ፥ በአሜሪካ፥ በካናዳና በአውስትራልያ ከተቋቋሙት ቀደምት አብያተ ክርስቲያናት መካከል የመጀመሪያው ቀዳማዊና ፋና ወጊው ቤተ ክርስቲያን የኮሎኝ ርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ነው።
ቤተክርስቲያናችን ወንጌልን በመላው ዓለም ማዳረስን ተልእኮ በማድረግ ለትምህርት ወደ አውሮፓ በመጡ አገልጋዮች ብርቱ ጥረት፣ በሊቀ ካህናት ዶክተር መርዓዊ ተበጀ እና በዲያቆን በዕደ ማርያም መርሻ ፊት አውራሪነት፥ በወቅቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ በነበሩት በአቡነ ተክለ ሃይማኖት መልካም ፈቃድ እና በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በ 1975 ዓ.ም በዚያን ጊዜ በጅቡቲና በምሥራቅ አፍሪካ ሊቀ ጳጳስ በነበሩት፥ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ የኖርዲክ እና ግሪክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በኾኑተ በብፁዕ አቡነ ኤልያስ ተባርኮ ተከፈተ።
አመሠራረቱም እንደሚከተለው ነው። በ 1971 ዓም ለሊቀ ካህናት ዶክተር መርዓዊ ተበጀ እና ዲያቆን በዕደ ማርያም መርሻ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ፈቃድ ወደ ጀርመን ለከፍተኛ ትምህርት ተላኩ። ወደ ጀርመን ሀገር በገቡ በሁለት ዓመት ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ለማቋቋም ጽንሰ ሀሳቡ በመርህ ደረጃ ለውይይት ቀረበ። በሃይደልበርግ ኗሪ ከሆኑ ወንድሞች ጋር በእመቤታችን ቅድስት ማርያም የጽዋ ማኅበር ስም መሰባሰብ ጀመሩ። ማኅበሩ የመገናኛ ድልድይ ሆኖ ሊያገለግላቸው ችሏል። በተለይም በ 1973 ዓ.ም. በምድረ ጀርመን በሃይደልበርግ ከተማ የመጀመሪያው ቅዳሴ ተቀደሰ። ለምእመናንም ቡራኬ ተሰጠ። በዚህም መንፈሳዊ አገልግሎት በለንደን ለጃማይካውያን መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት ተመድበው የነበሩት አባ አረጋዊ ወልደ ገብርኤል በኋላ የመላው አውሮፓ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ተገኝተዋል። ሥርዓተ ቅዳሴውንም መርተዋል። ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ካላቸው ፍቅርን ከተላበሰ ሰብእነታቸው የተነሣ መልካም ግንኙነት ነበራቸው። ቤተ ክርስቲያኑ ሲቋቋምም በበዓሉ ላይ ቤተ ክርስቲያናቸውን ወክለው ተገኝተዋል። የመጀመሪያው ቅዳሴ ከተካሄደ በኋላ ቤተ ክርስቲያን የማቋቋሙ ፍላጎት እየተጠናከረ መጣ። በሃይደልበርግና በሌሎች ከተማዎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተካፋዮች የሆኑባቸው የዘመን መለወጫ፥ የልደትና የትንሣኤ በዓላት ይከበሩ ጀመር።
የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ግንባታ

የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ግንባታ
በጀርመን አገር በኮለን ከተማ የምትገኘው ርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከዛሬ ቀደም ከነበራት ርስት የቦታ ባለቤትነት በእግዚአብሔር ፈቃድ ተጨማሪ የአምልኮ ፣ የበረከት ፣ የባለቤትነት ዕድሉን አምላከ ሚካኤል አሳክቶላት ከኃይል ወደ ኃይል ፣ ከበረከት ወደ በረከት ፣ ከትጥበት ወደ ስፋት ለመሻገር በባዕድ አገር ሰፊ የቦታ (1840 ካሬ ሜትር) ባለቤት ሆናለች ። የቤተክርስትያናችን የቦታ ግዢ ከተፈፀመ በኃላ በተያዘው እቅድ መሰረት የውስጥ ማሰፋፋት ለማድረግ አስፈላጊው ጥናት ለማድረግ ከአርክቴክት ጋር የመግባቢያ ውል ተፈርሞ ሰራው ተጀምሯል ቤተክርሰትያናችን በቅርሰነት ሰለተመዘገበ አፍርሶ መስራት ሰለማይቻል የቤተክርሰትያኑን ንድፍ ለማውጣት አስቸጋሪ ነበር። ሆኖም አስፈላጊው የግንባታ ሂደት አልፎ ለሚመለከታቸው የመንግሰት አካላት (Stadt Köln Bauamt) የመጀመሪያውን ማመልከቻ ( Bauantrag ) ተደርጐ ነበር ። ሆኖም ፍቃድ አግኝተን ለመስራት ከጐረቤቶቻችን ያለው እርቀት አስፈላጊ ነበር ይህም ምንአልባተ ግንባታው ሲጀመር በወሰን የሚጋሩን ጐረቤቶቻችን ቦታ ላይ ሊነካ ስለሚችል ( Baulast) የእነሱን ይሁንታ ማግኘት ነበረብን ነገር ግን ጐረቤቶቻችን ለዚህ ብዙ ገንዘብ ሰለጠየቁን ይህን ለማሰቀረት ከ Bauphysik ጋር በመመካከር Baulast ፕላኑ በውስጥ እንዴሆን ተደርጓል ከዚህ በተጨማሪ የመጀመሪያውን ቤተክርስትያን ግዢ ሲደረግ በፊት በኩል ባለው ጓሮ ቦታ ባለቤትነቱ የአኢቫንኬልሽ ቤ/ክረስትያን ይዞታ ሰለነበር ይህንም ቦታ ግዢ ተፈፅሞ የኖታሩ እማኝ አባሪ ተደርጐ ይህ ማሻሻያ የተደረገበት ማመልከቻ በድጋሚ ለStadt Köln Bauamt ተመልክቷል። የእንፃ መስሪያ እቅድ(Bauplan)ማሻሻያ በተደረገ ቁጥር ለአርክቴክቶሮቹ የሚከፈለው ገንዘብ እና ለቦታው መስሪያ ፍቃድ የማግኛው ጊዜ ብዙ ጊዜ ፈጅቷል ። አሁን የመስሪያ ፍቃድ ለማግኘት እየጠበቅን እንገኛለን::
ተጨማሪ ያንብቡየአገልግሎት መርሐ ግብር
ሳምንታዊ
ሥርዓተ ቅዳሴ
ወርሃዊ
ወርሃዊ ጸሎት
በቅርቡ የሚመጡ ዝግጅቶች

"የዚህ አጥቢያ መመሥረት ቤተ ክርስቲያን በሀገረ ጀርመንም ይሁን በመላው አውሮፓ ለደረሰችበት ደረጃ መሠረት የጣለ ነበር። ሊቀ ካህናት ዶ/ር መርዓዊ ተበጀ ከጀርመን አልፎ እንደ ጣልያን፣ ስዊድንና ፈረንሳይ የመሳሰሉት ሀገራት ቤተ ክርስቲያን ትመሠረት ዘንድ የተሳካ ሐዋርያዊ ጉዞ ያደረጉት ከዚህ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በመነሣት ነበር። በመኾኑም ዛሬ የአንጋፋውን የርእሰ አድባራት ኮለኝ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ክብረ በዓል ስናከብር የምናዘክረው በጀርመንና በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የተስፋፋችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሀገረ ጀርመን ኹነኛ መዋቅሯን ዘርግታ መንቀሳቀስ የጀመረችበትን መኾኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።"
- ብፁእ አቡነ ዲዮናስዮስ፥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርመንና አካባቢው እና የምሥራቅ ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
